በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከደቡብ ሱዳን ወደ ዩጋንዳ የተሰደዱ ከ1 ሚሊዮን መብለጡን ተመድ አስታወቀ


በጦርነት ከታመሰችው ደቡብ ሱዳን ወደአጎራባች ዩጋንዳ የተሰደዱት ዜጎቿ ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን መብለጡን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።

በጦርነት ከታመሰችው ደቡብ ሱዳን ወደአጎራባች ዩጋንዳ የተሰደዱት ዜጎቿ ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን መብለጡን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።

የመንግሥታቱ ድርጅት የሥደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ባለፈው የአንድ ዓመት ጊዜ በየዕለቱ አንድ ሺህ ስምንት መቶ ደቡብ ሱዳናውያን ዩጋንዳ መግባታቸውን ገልፀዋል። ሊሎች አንድ ሚሊዮን ደግሞ ወደኢትዮጲያ፣ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፖብሊክና ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፖብሊክ መሰደዳቸውን ጨምሮ ገልፀዋል።

በቅርብ ጊዜያት ስደተኛ ካምፖች የደረሱት ስደተኞች ሲቪሎችን በቁማቸው ቤታቸው ውስጥ በእሣት ማቃጠል ሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ ወሲባዊ ጥቃት ማድረስ እና ወንዶች ልጆችን ጠልፎ አስገድዶ ለተዋጊነት መመልመል የመሳሰሉ አረመኔያዊ ድርጊቶች ተፈፅመዋባቸዋል ብለዋል።

ለዚህ ዓመት ብቻ ስደተኞቹን የሚረዳበት ስድስት መቶ ሰባ አራት ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው የገለፀው የመንግሥታቱ ድርጅት እስካሁን የደረሰው ግን አንድ አምስተኛው ብቻ መሆኑን አመልክቱዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG