በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለም አቀፉ የፍልስት ድርጅት ካለፈዉ ወር ጀምሮ ከብዙ ሺህ በላይ የሚሆኑ ደቡብ ሱዳናዉያን ሰደተኞችን ወደ ኢትዮጵያ ማጓጓዙን አስታወቀ።


please wait

No media source currently available

0:00 0:04:09 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ካለፈዉ ወር ወር ጀምሮ አስራ አምስት ሺህ የሚሆኑ ደቡብ ሱዳናዉያን የእርስ በርስ ጦርነት ሸሽተተዉ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሲሆን በከባድ ረዥም ጉዞ ምክንያት በረሃብና በዉሃ ጥም በእጅጉ የተጎዱ መሆናቸዉን ዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ መስርሪያ ቤት ታዉቋል።

የድርጅቱ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ከፍተኛ የስራ ሃላፊ Gabriel Okeitoi እንዳብራሩት ጀልባና ተሽከርካሪ በመጠቀም ወደ አንድ መቶ አስራ ሰባት ኪሎ ሜትሮች ወይንም ስልሳ ሰባት ማይሎች ርቀት ሰደተኞቹን ልክቾር ወደሚባለዉ አዲስ የስደተኞች ካምፕ አጓጉዟል።

ብዙዎቹ ከደቡብ ሱዳን ማላካል ተነስተዉ እስከ አኮቦና ፓጋግ ድረስ ረጅም ርቀት ለአያሌ ቀናት በእግራቸዉ በሚያደርጉት ጉዞ የተጠሙ የተራቡ ሰለሆኑ ከፍተኛ የሰዉነት ፈሳሽ መቀነሰም እንደሚታይባቸዉ የተናገሩት በኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ፍልሰት ድርጅት ተወካይ ከተቀሩት ተባባሪ ድርጅቶች ጋር የጤና ክብካቤ እንክብካቤ እናደርግላቸዋለን ብለዋል።

ሙሉዉን ከመለስካቸዉ አመሃ ዘገባ ያድምጡ።
XS
SM
MD
LG