በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቭላድሚር ፑቲን እና የደቡብ ሱዳን መሪ በኃይል እና ንግድ ዙሪያ ተነጋገሩ


የሩሲያ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ከደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር፣ በሞስኮ ክሬምሊን ስብሰባ አድርገዋል እአአ መስከረም 28/2023
የሩሲያ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ከደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር፣ በሞስኮ ክሬምሊን ስብሰባ አድርገዋል እአአ መስከረም 28/2023

በሩሲያ ጉብኝት ላይ ያሉት የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር፤ ኃይል፣ ንግድ እና በተለይም ነዳጅ ዘይትን በተመከለተ ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን ግንኙነት በሚያስፋፉበት ጉዳይ ላይ ከፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተነገግረዋል።

የሩሲያ ኩባንያዎች በደቡብ ሱዳን የነዳጅ ማጣሪያ ቢመሠርቱ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት እንደሚያጠናክር ፑቲን መናገራቸውን የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

ፑቲን እና ኪር በተጨማሪም፣ በታሕሳስ 2017 ምርጫ ለማድረግ ባቀደችው ደቡብ ሱዳን ስላለው የፖለቲካ እና የጸጥታ ሁኔታ ተነጋግረዋል።

ደቡብ ሱዳን ነጻነቷን ከሱዳን ከተቀዳጀችበት ከእ.አ.አ 2011 ጀምሮ ሳልቫ ኪር ሀገሪቱን መርተዋል።

ሩሲያ ለኪር የጉብኝት ግብዣውን ያቀረበቸው፣ የዓለም ኃያላን ሀገራት ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈጸመችውን ወረራ በተመለከተ የአፍሪካ ሀገራትን ድጋፍ ለማግኘት በሚፎካከሩበት ወቅት መሆኑ ተነግሯል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG