በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት

ዩናይትድ ስቴትስ ብሪታንያ እና ኖርዌይ እኤአ የ2015ቱ የደቡብ ሱዳንን የሰላም ስምምነት እንዲያንሰራራ በቅርቡ አዲስ አበባ ላይ ለሚከፈተው ጉባዔ ድጋፍ ለመስጠት ያደረጉት ውሳኔ ያስደሰታቸው መሆኑን ደቡብ ሱዳናውያን ታጋዮችና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች አስታወቁ።

ዩናይትድ ስቴትስ ብሪታንያ እና ኖርዌይ እኤአ የ2015ቱ የደቡብ ሱዳንን የሰላም ስምምነት እንዲያንሰራራ በቅርቡ አዲስ አበባ ላይ ለሚከፈተው ጉባዔ ድጋፍ ለመስጠት ያደረጉት ውሳኔ ያስደሰታቸው መሆኑን ደቡብ ሱዳናውያን ታጋዮችና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች አስታወቁ።

ጉባዔው እንዲሳካ አሳታፊ መሆን እንዳለበት ሦስቱ ሃገሮች አሳስበዋል።

የ2015ቱን የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ወጭ የሸፈኑትና ያመቻቹት ሦስቱ ሃገሮች እንደነበሩ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ውሉ በተፈረመ በጥቂት ቀናት ውስጥ የመንግሥቱ ኃይሎችና የተቃዋሚ ታጣቂዎች ሁለቱም ተኩስ አቁሙን ማፍረሳቸው አይዘነጋም።

“ትሮኢካ” በሚል ቅፅል ስም የሚጠሩት ሦስቱ ሃገሮች ባወጡ መግለጫ በከፍተኛ ባለሥልጣናት ደረጃ በሚካሄደው የሰላም ውሉ ማነቃቂያ ጉባዔ ሁሉም ወገኖች ስምምነቱን እንደሚያከብሩ ቃል ገብተው እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG