በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን የርስ በርስ ጦርነት ለማብቃት የሰላም ሥምምነት ሊፈራረሙ ነው


የደቡብ ሱዳን ሽምቅ ተዋጊዎች መሪ ሪክ ማቻር ለአምስት ዓመታት የዘለቀውን የርስ በርስ ጦርነት ለማብቃት የታቀደውን የሰላም ሥምምነት እንደሚፈርሙ፣ አደራዳሪው ዛሬ አስታወቁ።

የደቡብ ሱዳን ሽምቅ ተዋጊዎች መሪ ሪክ ማቻር ለአምስት ዓመታት የዘለቀውን የርስ በርስ ጦርነት ለማብቃት የታቀደውን የሰላም ሥምምነት እንደሚፈርሙ፣ አደራዳሪው ዛሬ አስታወቁ።

ቀደም ሲል እርሳቸውና ሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ሥምምነቱን አንፈርምም ሲሉ፣ ሳልቫ ኪር ግን መፈረማቸው አይዘነጋም።

ማቻርና ፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር፣ የተኩስ አቁም ውልና የሥልጣን ክፍፍል ሥምምነት ባለፈው ወር ካርቱም ላይ ነበር የተፈራረሙት።

ዛሬ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ግን፣ ከአደራዳሪዎቻቸው ጋር ከብዙ ውይይት በኋላ“ማቻር አሳባቸውን ቀይረው ሥምምነቱን በፊርማቸው አፅድቀዋል” ሲሉ፣ የሱዳኑ ውጩ ጉዳይ ሚኒስትር አል ዳይረዲሪይ አሕመድ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

በዚህ ሥምምነት መሠረት ማቻር፣ በስደት ከሚገኙበት ደቡብ አፍሪካ ይመለሱና፣ በብሔራዊ የአንድነት መንግሥቱ ውስጥ፣ ከአምስቱ ምክትል ፕሬዚዳንቶች አንዱ ሆነው ያገለግላሉ ማለት ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG