በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጁባ ግጭት እንዲቆም ሳልቫኬር አዘዙ

ሳልቫ ኪር - የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት /ፎቶ - ፋይል/
ሳልቫ ኪር - የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት /ፎቶ - ፋይል/

ደቡብ ሱዳንን በብዙ ሺዎች ሕዝብ ወዳለቀበት የእርስ በእርስ ብጥብጥ ተመለሳ እንዳትገባ ያሰጋውና ሰሞኑን ከ150 በላይ ሰው የተገደለበት ግጭት በፋጣኝ እንዲቆም ፕሬዝዳንት ሳልቫኬር ዐዋጅ አስነገሩ።

ደቡብ ሱዳንን በብዙ ሺዎች ሕዝብ ወዳለቀበት የእርስ በእርስ ብጥብጥ ተመለሳ እንዳትገባ ያሰጋውና ሰሞኑን ከ150 በላይ ሰው የተገደለበት ግጭት በፋጣኝ እንዲቆም ፕሬዝዳንት ሳልቫኬር ዐዋጅ አስነገሩ።

ዛሬ የወጣው “የጠብ ማስቆሚያ ዐዋጅ” ጎራ ለይተው እየተታኮሱ ያሉት ተቃዋሚ ወገኖች በጁባ ሰዓት አቆጣጠር እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ብረት እንዲያወርዱ ያዛል።

የሁለቱም ጎራ የጦር አዛዦች ተዋጊዎቻቸውን እንዲቆጣጠሩ፣ የሲቪሎች ሕይወት ለአደጋ አለመጋለጡን እንዲያረጋግጡና በተዋጊዎቻቸው ዒላማ የሚደረጉ የጎሳ ቡድኖች ካሉም ጥበቃ እንዲያደረግላቸው የፕሬዝዳንቱ ዐዋጅ ያሳስባል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

የጁባ ግጭት እንዲቆም ሳልቫኬር አዘዙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:38 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG