ዋሺንግተን ዲሲ —
በደቡብ ሱዳን ለበርካታ ዓመታት በተካሄዱ ጦርነቶች በመላ ሃገሪቱ የተዘሩ መሬት ውስጥ የተቀበሩ ቦምቦች ሌሎችም ፈንጂዎች ይገኙባቸዋል። አሁንም ያልተወገዱት ፈንጂዎች በአርሶ አደሮች እና በሌሎችም ማኅበረሰቦች ላይ አደጋ እንደሚደቅኑ የተናገረው የመንግሥታቱ ድርጅት የፈንጂ ማፅዳት አገልግሎት የተቀሩትን በስድስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ይወገዳሉ ብሎ እንደሚጠብቅ ገልጿል ።
በአሁኑ ጊዜ ደቡብ ሱዳን ውስጥ ፈንጂ ያለባቸው ተብለው የሚያሰጉት አካባባኢዎች በሃያ ሰባት ካሬ ኪሎሜትር ስፋት ለመቀነስ መቻሉን የመንግሥታቱ ድርጅት አገልግሎት አስታውቁዋል።
በተጠቀሰው የስድስት ዓመት ጊዜ ፈንጂዎቹን ሙሉ በሙሉ እንናስወግዳለን ብለን ተስፋ ባንደርግም ይህን እውን ለማደረግ የነዋሪዎች አስተዋጽዖ አስፈላጊ መሆኑን ነው የደቡብ ሱዳን ብሄራዊ የፈንጂ አስወጋጅ መሥሪያ ቤት ተጠሪ ጃሩክ ባራክ ጃሩክ ያስገነዘቡት።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ