በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ሱዳን የተደረሰው የሰላም ሥምምነት ፈተናዎች


ፕሬዚዳንት ሣልቫ ኪር
ፕሬዚዳንት ሣልቫ ኪር

በደቡብ ሱዳን እንደገና የተደረሰውን የሰላም ሥምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ብዙ ፈተናዎች ተደቅነዋል - አብዛኛው ግን የዓለምቀፉ ማኅበረሰብ ጥርጣሬ ስላደረበት ነው ይላሉ ፕሬዚዳንት ሣልቫ ኪር።

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ትላንት ጁባ ውስጥ ለተሰበሰቡ በመቶዎች ለተቆጠሩ የደቡብ ሱዳን ሕዝብ ዓርነት እንቅስቃሴ የ/ኤስፒኤልኤም/ ካድሬዎች ሲናገሩ፣

“በመከረም ወር የተደረሰው ሥምምነት ጥሩ አልነበረም የፈረምኩት ግን የሕዝብ ስቃይ እንዲቀጥል ባለመፈለጌ ነው” ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ኪር ቀደም ሲል ከገዢው ፓርቲ ሕግ አርቃቂዎች ጋር ተገናኝተው፣ የተደረሰውን ሥምምነት ተግባራዊ ለማድረግ መንግሥት በቂ ገንዘብ የለውም ብለዋል።

/TROIKA/ በመባል የሚጠራው - ዩናይትድ ስቴትስ፣ ኖርዌይና ብሪታንያ የሚገኙበት ቡድን - ሥምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ መንግሥት የራሡን የኃብት ምንጭ እንዲጠቀምና ሂደቱ እንዲቀጥል የፖለቲካ ፍላጎቱ ካለው እንዲያሳይ በተደጋጋሚ መክሯል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG