በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር ስለ ዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀብ


የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር ማይክል ማኩዌ
የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር ማይክል ማኩዌ

ዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀብ ብትጥልብኝም በአደባባይ የፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር መንግሥትን ወክዬ መናገሬን አልተውም ሲሉ የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር ማይክል ማኩዌ ተናገሩ።

ዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀብ ብትጥልብኝም በአደባባይ የፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር መንግሥትን ወክዬ መናገሬን አልተውም ሲሉ የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር ማይክል ማኩዌ ተናገሩ።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው መስከረም ሥድስት ቀን ባወጣው መግለጫ የማስታወቂያ ሚኒስትር ማኩዌን የደቡብ ሱዳንን ሰላም ፀጥታና መረጋጋት አደጋ ላይ በሚጥል ተግባር በመሳተፍ ወንጅሉዋቸዋል።

ማኩዌ ለቪኦኤ የደቡብ ሱዳን ክፍል ለመጀመሪያ ጊዜ ስለማዕቀቦቹ በሰጡት ቃል የትረምፕ አስተዳደር በወሰደው ርምጃ አልሸማቀቅም፣ የማስታውቂያ ሚኒስትርነት ሥራዬን ነው የምሠራው ብለዋል።

የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ባለቤትና ልጆቻቸው ደቡብ ሱዳን ከመገንጠሏ አስቀድሞ በሃያ አንድ ዓመቱ የሱዳን የርስ በርስ ብጥብጥ ውቅት ወደዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ ሲሆን ሚኒስትሩ ማዕቀቡ ቤተሰባቸውን መጥተው መጎብኘት እንደሚከለክላቸው አላስተባበሉም።

“የግድ አሜሪካ ካልሄድኩ አልልም ቤተሰቦቼ ሊያዩኝ ከፈለጉ መጥተው ሊያዩኝ ይችላሉ” ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG