በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢጋድ አባል ሀገሮች በንግድ፣ በቀረጥ እና በመገናኛ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ


የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ክልላዊ የልማት በይነ መንግሥታት ባለልሥልጣን (ኢጋድ) አብዛኞቹ አባል ሃገሮች፣ ዜጎቻቸው በአባል ሃገሮች ውስጥ በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ የቀረበውን ሃሳብ ይደግፋሉ፡፡ ችግሩ ደቡብ ሱዳን ነገሩ ስላልጣማት እምቢታዋን መቀጠሏ ነው።

የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ክልላዊ የልማት በይነ መንግሥታት ባለልሥልጣን (ኢጋድ) አብዛኞቹ አባል ሃገሮች፣ ዜጎቻቸው በአባል ሃገሮች ውስጥ በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ የቀረበውን ሃሳብ ይደግፋሉ፡፡ ችግሩ ደቡብ ሱዳን ነገሩ ስላልጣማት እምቢታዋን መቀጠሏ ነው።

ሥምንት አባል ሃገሮች ያሉት ኢጋድ ባለሥልጣናት እና ዲፕሎማቶች በዚህ ሳምንት ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ላይ ተሰብስበው በጉዳዩ ላይ መክረዋል። በንግድ በቀረጥ እና በመገናኛ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በደቡብ ሱዳን የኢጋድ የተጠባባቂ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ አብደልራሂም አህመድ ኻሊል በክልሉ ለአባል ሃገሮች ዜጎች ቪዛ እንዳያስፈልግ ቢደረግ የምጣኔ ሃብት ዕድገት እንደሚያበረታታ ገልፀዋል።

በደቡብ ሱዳን የአውሮፓ ሕብረት ልዑካን ቡድን መሪ ስቴፋኖ ደ ሊዮ በበኩላቸው የይለፍ ፈቃድ ሳያስፈልግ መዘዋወሩ አባል ሃገሮቹ አንድነት አንድነት እንዲፈጥሩ ይጠቅማል ብለዋል።

በርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ያለችው የደቡብ ሱዳን ባለልሥልጣናት ግን በሃሳቡ ያን ያህል አልተደሰቱም።

በአፍሪካ ሕብረት እና በኢጋድ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ዴቪድ ቡዎም ቾት የአባል ሃገሮቹን ድንበር ክፍት ማድረግ የመከላከያ ችግር ያመጣል ሲሉ ተከራክረዋል። የአገር ወስጥ ደኅንነት ሚኒስትሩም የደቡቡ ሱዳን ሕዝብ ሰባ ከመቶው ያልተማረ በመሆኑ፣ በአባል ሃገሮች ውስጥ በነፃነት መዘዋወር መፈቀዱ ምንም አይጠቅምም ብለዋል።

ሥራ ፍለጋ ወደ ኢትዮጵያ አይሄዱ፣ ኬንያም ይሁን ዩጋንዳ አይሄዱም ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG