በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ሱዳን ጎርፍ የ700 ሺሕ ሰዎችን ሕይወት አመሳቀለ


በምስራቅ ሱዳን የተከሰተውን ከባድ የጎርፍ አደጋ ተከትሎ በቀይ ባህር ግዛት ቶካር የሱዳን ጦር ወታደሮች በተጥለቀለቀ አካባቢ በጀልባ ሲጠቀሙ፤ መስከረም 5/2024
በምስራቅ ሱዳን የተከሰተውን ከባድ የጎርፍ አደጋ ተከትሎ በቀይ ባህር ግዛት ቶካር የሱዳን ጦር ወታደሮች በተጥለቀለቀ አካባቢ በጀልባ ሲጠቀሙ፤ መስከረም 5/2024

በደቡብ ሱዳን በመድረስ ላይ ያለው የጎርፍ አደጋ ከ700 ሺሕ በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ለችግር እንደዳረገ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታውቋል።

ጎርፍ የመኖሪያ ቤቶችን፣ ሰብል እና መሠረተ ልማቶችን ሲያወድም፣ የትምህርትና የጤና አገልግሎቶች እንዲቋረጡ ማድረጉን፣ በሽታም እንዳይዛመት ሥጋት መፍጠሩን በተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) ትላንት ሐሙስ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።

ጎርፍ፤ በሃገሪቱ ከሚገኙ 78 አውራጃዎች ውስጥ 38 በሚሆኑት የሚገኙ ከ710 ሺሕ በላይ ነዋሪዎችን ሕይወት ለአደጋ ማጋለጡን ቢሮው አስታውቋል።

ደቡብ ሱዳን ለአሥርተ ዓመታት ያላየችው የጎርፍ አደጋ እንደገጠማት የረድኤት ድርጅቶች በማስታወቅ ላይ ሲሆኑ፣ ኦቻ በበኩሉ ተረጂዎችን መድረስ እንዳልቻለ ገልጿል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG