ዋሺንግተን ዲሲ —
አብየ ያለው የተባበሩት መንግሥታ ድርጅት ጊዜያዊ የፀጥታ ኃይል ቃል አቀባይ ዳንኔል አዴኬራ ኮሎም በተባለው መንደር በደረሰው ጥቃት 15 አስከሬኖች መቁጠራቸውን ተናግረዋል። ኮሎም ከአብየ በስተሰሜን 12 ኪሎሜትር ርቆ ይገኛል።
ወታደሮቻችን ባረጋገጡት መሰረት 15 ሰዎች ሲሞቱ፣ 3 ልጆች የገቡበት አልታወቀም። 25 ቆስለዋል። 19 መኖርያ ቤቶች በእሳት ጋይተዋል ሲሉ ቃል አቀባዩ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።
ትላንት ጥቃት የተከፈተው በጎሳዎች መካከል በሚካሄደ የበቀል ግጭት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል አዴኬራ ጠቁሟል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ