ማላካል፤ ቦር፣ ጁባ፣ አዲስ አበባ፣ ናይሮቢ፣ ዋሺንግተን ዲ.ሲ. —
የደቡብ ሱዳን መንግሥት በሃገሩ እየተካሄደ ያለውን የጎሣ ግጭት ሊገታ የሚችል የተኩስ አቁም ውል ለማድረግ መስማማቱ ተገልጿል፡፡
የምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች የልማት ትብብር ተቋሙ ኢጋድ ይህንን ይፋ ያደረገው ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ ለሁለት ቀናት የተካሄደው ውይይት የዓርብ ታኅሣስ 18/2006 ዓ.ም የሁለተኛ ቀን ውሎው ሲጠናቀቅ ነው፡፡
ኢጋድ በዚሁ መግለጫው የድሞው ምክትል ፕሬዚዳንትና የአሁኑ ተቀናቃኝ ሪያክ ማቻርም ለተኩስ ማቆሙ ተመሣሣይ ቃል እንዲገቡ አሳስቧል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ደቡብ ሱዳን ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን አሁንም የሚገኙት በአሣሣቢ ሁኔታ ውስጥ መሆኑን ዛሬም ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ በሃገሪቱ ውስጥ ሰላም እንዲመለስ እያደረገ ላለው ጥረት የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር፣ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ጁባ ሄደው ከፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋር መነጋገራቸውን ጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም ከጆንግሌ ዋና ከተማ ቦር ሦስት መቶ ኢትዮጵያዊያን ወደ ጁባ፣ ሌሎች ስምንት መቶ ከዩኒቲ ስቴት ዋና ከተማ ቤንቲዩ ወደ ሃገር ለመመለስ ወደ ሱዳን ሄግሊጅ መወሰዳቸውን፣ 650 የሚሆኑ በጋምቤላ በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለቪኦኤ ገልጿል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ሁከት በበረከተባቸው የደቡብ ሱዳን አካባቢዎች ግድያ፣ ዘረፋና መድፈርን የመሣሰሉ ብርቱ ጥቃቶች እየተፈፀሙ መሆኑንና የውጭ ዜጎች ዒላማ መደረጋቸውን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየደረሷቸው መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን ልዑክ ኃይል - ኡንሚስ ቃል አቀባይ ጆ ኮንትሬራስ ለቪኦኤ ገልፀው ጉዳዩን የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኤክስፐርቶች ቀንና ሌሊት በቅርበት እያጠኑና እየተከታተሉ መሆናቸውን ለቪኦኤ አስረድተዋል፡፡
ለጥቃት ለተጋለጡት ለኢትዮጵያዊኑና ለኤርትራዊያንም ለመድረስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን፣ እስከአሁን በሁሉም የመንግሥታቱ ድርጅት ግቢዎች ውስጥ ከተጠለሉት 63 ሺህ የሚሆኑ ሲቪሎች መካከልም ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን እንደሚገኙ፣ ኃይሉ ባሉት አራት ሄሊኮፕተሮች እየተጠቀመ የተከበቡትን ለማውጣት እየተጣደፈ መሆኑን ኮንትሬራስ ገልፀዋል፡፡
ለዝርዝር መረጃ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡