ካርቱም ላይ የሥልጣን ክፍፍል ሥምምነት ላይ ከደረሱት የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል አንዳንዶቹ በሥምምነቱ በተካተቱት በአንዳንዶቹ አንቀፆች ባንስማም የፈረምነው ለሰላም ዕድል ስንል ነው ይላሉ፡፡
ሆኖም ኢጋድ ማለት የምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን ትናንት ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ የተጠናከረ የሰላም ውል እስኪደረስ ፕሬዚዳንት ኦመር ሃሰን አል በሺር ከሚገኙበት ከሱዳን ሸምጋዮች ቡድን ጋር ሆኖ ድርድሮቹን ማስተባበሩን እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡
በኢጋድ መግለጫ መሰረት የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ለካርቱሙ የሰላም ሂደት ቀጣይነት ድጋፍ የሚሰጥ የኤክስፐርቶች ቡድን ይልካሉ። የድርድሩ ሥፍራ ይለወጣል የሚሉ ሪፖርቶች ስናፈሱ ቆይተዋል፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ