በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ሱዳን ሰዓት እላፊ አወጀች


ፎቶ ፋይል፡ የደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ፣ ጁባ
ፎቶ ፋይል፡ የደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ፣ ጁባ

የደቡብ ሱዳን ፖሊስ የምሽት ሰዓት እላፊ አውጇል። ፖሊስ ሰዓት እላፊውን ያወጀው ትላንት ጠዋት ሱዳናውያንን በመቃወም የተደረገው ሰልፍ ወደ ዘረፋ በማምራቱ ነው። ለተቃውሞው መነሻ የሆነው 29 ደቡብ ሱዳናውያን በዚህ ሳምንት በሱዳን ተገድለዋል በሚል እንደሆነ የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

የሱዳን ሠራዊት ዋድ ማዳኒ የተሰኘችውን ከተማ ከፈጥኖ ደራሽ ኅይሉ ቁጥጥር ነጻ ካወጣ በኋላ ሲቪሎችን ገድሏል የሚል ክስ ቀርቦበታል። ጦርነቱ በሚያዚያ ወር 2015 ዓ/ም ከጀመረ ወዲህ ከታዩት ዘግናኝ ክስተቶች አንዱ እንደሆነም ተነግሯል። ከሟቾቹ ውስጥ ደቡብ ሱዳናውያን ይገኙበት እንደሁ በገለልተኛ ወገን አለማረጋገጡን ኤኤፍፒ አመልክቷል።

በኢንተርኔት ላይ የወጡ ምስሎች የሐሙሱን ተቃውሞ እንደቀሰቀሱ ሲታወቅ፣ ሰልፈኞች ሱቆችን ወደ መዝረፍ ሲያምሩ ፖሊስ የማስጠንቀቂያ ተኩስ መክፈቱ ታውቋል። ተቃውሞው በመዲናዋ ጁባና በሌሎች ሶስት ከተሞች እንደተካሄደም ታውቋል።

በሱዳን በመካሄድ ላይ ያለው ጦርነት በአሥር ሺሕ የሚቆጠር ሕይወት ሲቀጥፍ፣ 12 ሚሊዮን የሚሆኑትን ክመኖሪያቸው አፈናቅሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG