በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ሱዳን የዋይት ሃውስን መግለጫ ነቀፈች


የደቡብ ሱዳን መንግሥት የሥልጣን ዘምኑን በተጨማሪ ሦስት ዓመት ለማራዘም የወሰደውን እርምጃ በማውገዝ የሀገሪቱ መሪዎች የሰላም ሥምምነት ላይ ለመድረስ ከልብ እንዲደራደሩ የጠይቀውን የዋይት ሃውስ መግለጫ ጁባ ነቀፈች።

የደቡብ ሱዳን መንግሥት የሥልጣን ዘምኑን በተጨማሪ ሦስት ዓመት ለማራዘም የወሰደውን እርምጃ በማውገዝ የሀገሪቱ መሪዎች የሰላም ሥምምነት ላይ ለመድረስ ከልብ እንዲደራደሩ የጠይቀውን የዋይት ሃውስ መግለጫ ጁባ ነቀፈች።

የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ሳራ ሃከቢ ሳንደርስ ከትናንት በስተያ ዕሁድ በወጡት መግለጫ የደቡብ ሱዳን መሪዎች ሲቪል ማኅበረሠቦችን አብያተ ክርስቲያናት ሴቶችንና ሌሎችንም ካሁን ቀደም የተገለሉ ወገኖች ያሳተፈ ድርድር እንዲያካሂዱ ዩናይትድ ስቴትስ አሳስባለች።

በልሂቃን ብቻ የሚደረግ የጠበበ ሥምምነት ዞሮ የሌላ ግጭት ዘር ከመዝራት ሌላ ፋይዳ አይኖረውም ብሉዋል መግለጫው።

ፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር እና የአማፅያኑ መሪ ሪያክ ማቻር ለሀገሪቱ እውነተኛ ሰላም የሚያስፈልገውን አመራር አላሳዩም ሲል መግለጫው ነቅፏል። መሪዎቹ ለሰላም ለመልካም አስተዳደርና ለገንዘብ ተጠያቂነት ቁርጠኝነት ካላሳዩ ዩናይትድስ ስቴትስ ለሽግግር መንግሥቱ ዋስትናም ሆነ የገንዘብ ድጋፍ አታደርግም። ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ተጨማሪ ድጋፍ እንዲያገኝ አትሟገትም ብሉዋል።

የደቡብ ሱዳን መንግሥት ትናንት በሰጠው ምላሽ ዩናይትድ ስቴትስ እንደኛ ላለ ወዳጅዋ እንዲህ ያለ ነቀፌታ መሰንዘር አይጠበቅባትም ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG