በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን የጦር ኃይል ከመፈንቅለ መንግሥቱ ሙከራ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ መኮንኖችን አሰረ


የሱዳን የጦር ኃይል ከከሸፈ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በተያያዘ የጦር ሰራዊቱን ዋና አዛዥ እና ሌሎች በርካታ ከፍተኛ መኮንኖችን አስሯል።

የጦር ኃይሉ ትናንት ረቡዕ ማታ ባወጣው መግለጫ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹሙን ጀኔራልሃሺም አብደል ሙታሊብ ባባካር እና ቢያንስ አስራ ሁለት ከፍተኛ መኮንኖችን አስረናል ብሏል።

የመንግሥቱ የዜና አገልግሎት ሱና ባሰራጨው ዜና ፡ የብሄራዊ ሥለላ እና ፀጥታ አገልግሎት፡ የእስላማዊ ንቅናቄ እና የብሄራዊ ኮንግሬስ ፓርቲ መሪዎች ከመፈንቅለ መንግሥቱ ሴራ በተያያዘ ተወንጅለዋል ብሉዋል።

ሱዳን ውስጥ መፈንቅለ መንግሥት ተሞከረ ሲባል በዚህ በሃምሌ ወር ብቻ ሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው። የረጅም ጊዜው የሀገሪቱን መሪ ኦመር አል በሽር ባለፈው ሚያዝያ ወር አውርዶ መሪነቱን የያዘው ወታደራዊው ምክር ቤት እ ኤ አ ሃምሌ አስራ አንድ ቀን በተጠነሰሰ የመፈንቅለ መንግሥት ሴራ አስራ ስድስት ሥራ ላይ ያሉና ጡረተኛ ወታደራዊ መኮንኖችን አስረናል ማለቱ ይታወሳል።

ትናንት የታሰሩት ጄነራል ባባካር አምባ ገነኑ መሪ አል በሺር ከሥልጣን ከተወገዱ ከጥቂት ቀናት በኋላ ነበር የጦር ኃይሎች ኤታ ማዦር ሹም ሆነው የተሾሙት።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG