በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ሱዳን የተኩስ አቁም ውል እንዲያከብሩ ተጠየቀ

በደቡብ ሱዳን ግጭት ውስጥ የሚሳተፉት ወገኖች በሙሉ ከአንድ ወር በፊት የተፈረመውን የተኩስ አቁም ውል እንዲያከብሩ የሀገሪቱን የሰላም ሥምምነት ተፈፃሚነት የሚቆጣጠረው አካል አሳሰበ።

በደቡብ ሱዳን ግጭት ውስጥ የሚሳተፉት ወገኖች በሙሉ ከአንድ ወር በፊት የተፈረመውን የተኩስ አቁም ውል እንዲያከብሩ የሀገሪቱን የሰላም ሥምምነት ተፈፃሚነት የሚቆጣጠረው አካል አሳሰበ።

የሰላም ሥምምነቱ የጋራ ተቆጣጣሪና ገምጋሚ ኮሚሽን ሊቀ መንበር ፌስቱስ ሞጋዬ ትናንት ሰኞ ባወጡት መግለጫ በመንግሥቱና በሽምቅ ተዋጊዎቹ መካከል የተፈረመው ተኩስ አቁም እየተዳከመ መሆኑን ፍንጭ ሰጥተዋል። የተኩስ አቁሙ ዓላማ እኤአ ከ2013 መጨረሻ አንስቶ አራት ሚሊዮን ህዝቡዋን ያፈናቀለው የፖለቲካና የብሄረሰብ ግጭት እክትሞ ሰላም እንዲሰፍን መሆኑ ተመልክቱዋል።

የደቡብ ሱዳን መንግሥት እና ተቃዋሚዎቹ ከአንድ ወር በፊት አዲስ አበባ ላይ የተፈረመውን የተኩስ አቁም በመጣስ እርስ በርሳቸው እየተወነጃጀሉ ናቸው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG