በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚዎች መንግሥቱን ፀብ በማጫር እየከሰሱ ነው


በደቡብ ሱዳን መንግስት ተኩስ የማቆም ስምምነቱን በመጣስ በይዞታዎቻችን ላይ ጥቃት እየፈጸመ ነው ሲሉ ተቃዋሚዎች እየወነጀሉ ነው።

ይደግፉት የነበሩት የዩጋንዳ ወታደሮች በሠላም ስምምነቱ መሠረት ሰለሚወጡ “መንግሥቱ በተቻለ መጠን ተጨማሪ ይዞታዎችን ለመቆጣጠር እየሞከረ ነው” ብለዋል።

የተቃዋሚዎቹ ቃል አቀባይ ዲክሰን ጋትሉአክ ጆን ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “አሁን እዚህ እየተነጋገርን ባለንበት ሰዓት መንግሥት የጥቃት እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፤ የጁባ መንግሥት በምሥራቅ ኢኳቶሪያና ውድሩባ በሚባሉ ቦታዎች ባሉ ይዞታዎቻችን ላይ ጥቃት እየፈፀመ ነው” ብለዋል፡፡

በማርዲም የተወሰነ ግጭት እንዳለና መንግሥት ፓጁት በሚባለው የጆንግሌ ግዛት አካባባቢ ጦሩን አያዘጋጀ መሆኑን ዲክሰን ተናግረዋል፡፡

ቃል አቀባዩ አክለውም “ዋናው ዓላማቸው የዩጋንዳ ወታደሮች እየወጡ ባሉበት ሁኔታ ተጨማሪ ቦታዎችን መያዝ ነው፤ እናም ከዚህ በመነሣት መንግሥት በፓጁት አድርጎ አኮቦን ለማጥቃት እየተዘጋጀ ይገኛል። ትናንትናም ዩኒቲ ግዛት ውስጥ በሚገኙት ቶኖትና ግሊኝ ይዞታዎቻችን ላይ ጥቃት ፈፅመዋል” ብለዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚዎች መንግሥቱን ፀብ በማጫር እየከሰሱ ነው 2'23"
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:32 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG