ዋሺንግተን ዲሲ —
የደቡብ ሱዳን ወታደሮች በዩኒቲ ክፍለ ሃገር በዚሁ የአውሮፓውያን ዓመት ውስጥ በአካሄዱት ጥቃት ህፃናትና አረጋውያንን በቁማቸው አቃጥለዋል፣ ሴቶችን ደፍረዋል፣ ሲቪሎችን በጥይትና በብረት ለበስ ተሽከርካሪዎቻቸው እየዳጡ ገድለዋል ሲል አምነስቲ ኢንተርናሺናል ባወጣው አዲስ ሪፖርት ወነጀለ።
የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ ትናንት ረቡዕ ባወጣው አዲስ ሪፖርት የደቡብ ሱዳን መንግስት ከሱዳን በሚያዋስነው ዩኒቲ ክፍለ ሀገር ወታደራዊ ዘመቻውን የከፈተው ባለፈው ሚያዝያ አጋማሽ ላይ እንደሆነ እና ለሁለት ወራት እንደቀጠለ አመልክቱዋል።
በዚያ ሁሉ መሃል ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና የቀድሞ ምክትላቸው የነበሩት የአማፅያን መሪው ሪያክ ማሻር ባለፈው ሳምንት ረቡዕ በተፈራረሙት የሰላም ሥምምነት ላይ እየተደራደሩ እንደነበር አምነስቲ አያያዞ ገልጿል።
የደቡብ ሱዳን የጦር ሰራዊት ቃል አቀባይ ሜጀር ጄኔራል ሉል ሩዋይ ኮኣንግ ሪፖርቱን አስተባብለዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ