በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ሱዳን ለዕርዳታ ፈላጊዎች ዕርዳታ ለማድረስ እንቅፋት እንደገጠው ተመድ አስታወቀ


በደቡብ ሱዳን ሁከት፣ ዝርፊያ፣ ጠለፋና ማስፈራራት በሰባት ሚሊዮን የሚገመቱ ዕርዳታ ፈላጊዎችን ለመድረስ እንቅፋት ሆነዋል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የረድዔት ሠራተኞችን አያያዝ አውግዟል።

በደቡብ ሱዳን ሁከት፣ ዝርፊያ፣ ጠለፋና ማስፈራራት በሰባት ሚሊዮን የሚገመቱ ዕርዳታ ፈላጊዎችን ለመድረስ እንቅፋት ሆነዋል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የረድዔት ሠራተኞችን አያያዝ አውግዟል።

በዓለሙ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሃፊ ማርክ ሎውኮከ ሲናገሩ ባለፉት ሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ 4 የረድዔት ሠራተኞች ተገድለዋል፣ ሌሎች 10 ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል። ባለሥልጣኑ የሰጧቸው አሃዞች ምሥራቅ ያንጊሪ ከተማ አቅራቢያ የተጠለፉትን ሁለት ሠራተኞች አይጨምርም።

በያዝነው ሣምንት ውስጥ ደቡብ ሱዳንን የጎበኙት ማርክ ማርክ ሎውኮከ አክለው እንደገለጹት - ሁለቱም ማለት መንግሥቱና ታጣቂ ተቃዋሚዎች፣ ግጭቶችን ለማስቆም በቂ ጥረት አላደርጉም፣ የረድዔት ሠራተኞች ተረጂዎችን ለመድረስ እንቅፋት የሆኑ ኃይሎቻቸውን ማስቆም አልቻሉም።

“የኛ ፍላጎት፣ ሁሉንም ተረጂዎች ለመድረስ ፈጣን፣ አስተማማኝና እንቅፋት የሌለበት ሁኔታ እንዲፈጠር ነው” ብለዋል - የዓለሙ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሐፊ ማርክ ሎውኮከ፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG