አዲስ አበባ —
አዲሳባ ላይ እየተወያዩ የሚገኙት የደቡብ ሱዳን መንግሥትና ተቃዋሚዎች፣ ዋና ከተማዋ ጁባ ላይ በሚሰፍረው የፖሊስ ኃይል ቁጥር ተስማምተዋል። በዚሁ መሠረት ተቃዋሚዎቹ ባለፈው መስከረም በመንግሥትና እራሳቸውን «የቀድሞ ታሳሪዎች» ብለው በሚጠሩት ሚኒስትሮች የተፈረመውን ሰነድ ዛሬ አጽድቀዋል።
የተለያዩ ተቋማትን ለመጠበቅ በሚሰማሩት ፭ ሺህ ወታደሮች ስብጥር ላይ ግን ገና ተጨማሪ ውይይት እንደሚያደርጉ ነው የተስማሙት።
እስክንድር ፍሬው ዝርዝሩን ዘግቧል። ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።