በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መንግሥት በደቡብ ክልል የህግ የበላይነትን እንዲያስከብር ነዋሪዎች ጠየቁ


መንግሥት በደቡብ ክልል የህግ የበላይነትን እንዲያስከብር ነዋሪዎች ጠየቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:46 0:00

መንግሥት በደቡብ ክልል የህግ የበላይነትን እንዲያስከብር ነዋሪዎች ጠየቁ

በደቡብ ክልል የተለያዩ ጥቃቶች በፈፀሙና ግጭቶች በፈጠሩ ወንጀለኞች ባሏቸው ግለሰቦች ላይ መንግሥት እርምጃ እንዲወስድና የህግ የበላይነት እንዲያስከብር ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የክልሉ ነዎሪዎች ጠየቁ።

መንግሥት እየወሰድኩ ነው የሚለውን እርምጃ አንዳንዶች ወንጀለኛውን ከንፁሃን ያልለየ አፈሳና የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈፀምበት ሲሉ የሚከስሱ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ሁነኛ እርምጃ ሳይሆን ፖለቲካዊ ይዘት ያለው የይምሰል ሥራ ነው የሚሰራው በማለት ኮንኗል።

በሌላ በኩል ደግሞ መንግሥት በክልሉ ያለውን የፀጥታ ችግር በአንድ ወር ውስጥ እፈታቸዋለሁ ሲል ያስቀመጠው አቅጣጫ የዜጎችን መብት ለመጣስ በር ይከፍታል የሚል ሥጋት ፈጥሮብናል ያሉ ሲሆን ገሚሶቹ ደግሞ ከንግግር ያለፈ፤ ተፈፃሚና በውጤት የተደገፈ እንዲሆን አሳስበዋል።

በወንጀል የጠረጠራቸውን ከ1ሺህ በላይ ሰዎችን ማሰሩን ያስታወቀው የክልሉ የፀጥታ ምክር ቤት ሰብሳቢ እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው ክልሉን የግጭት ማዕከል እያደረጉ ነው ባሏቸው ቡድኖች ላይ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል ሲሉ ሰሞኑን በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ በተደረገ ምክክር አስታውቀዋል።

ዘገባው የዮናታን ዘብዴዎስ ነው።

XS
SM
MD
LG