ዋሺንግተን ዲሲ —
ሰሜን ኮሪያ በኑክሊየር ጦር መሣሪያ ማፅዳት አቋሟ ከፀናች፣ መንግሥታቸው ወታደራዊ ጫናውን ቀለል እንደሚያደርግ፣ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ሙን ጄ-ኢን ዛሬ ሐሙስ ተናገሩ።
የፕሬዚዳንት ሙን ቢሮ ይፋ ባደረገው መሠረት፣ ሰሜን ኮሪያ የኑክሉየር ተቋሟን ካወደመችና ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የጀመረችውን ውይይት ከገፋችበት፣ የጋራ መግባባት የሚጀመርበት ሁኔታ ሊመቻች ይችላል።
ሙን አክለውም፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የሚካሄደውን ወታደራዊ ልምምድ ለማቋረጥ እንደሚያስቡበትም አመልክተዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ