የደቡብ ኮሪያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሀገሪቱን ፕሬዝደንት ዩን ሶክ ዮል ለመክሰስ ለፓርላማው ሐሳብ አቅርበዋል።
ፕሬዝደንቱ በአጭሩ የተቀጨውን ወታደራዊ ሕግ ማወጃቸውን ተከትሎ ሥልጣን እንዲለቁ ግፊት ጨምሯል።
ዩን ሶክ ዩል ትላንት ወታደራዊ ሕግ እንዳወጁ፣ እንደራሴዎች ዐዋጁን ውድቅ እንዳያደርጉ የፀጥታ ኃይሎች ፓርላማውን ከበው ነበር። ፕሬዝደንቱ ሥልጣን እንዲለቁ እና ወታደራዊ ሕጉንም በአስቸኳይ እንዲሽሩ በፓርላማው ዓባላትና በሕዝቡም የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዶ ነበር።
ዩን ወታደራዊ ዐዋጁን ባስታወቁበት ማክሰኞ ምሽት፣ "ፀረ መንግሥት" ብለው የጠሯቸውን ኃይላት እንደሚያጠፉ ዝተው፣ ባለቤታቸውን ጨምሮ ቁልፍ የመንግስት ባለሥልጣናት ፈጽመዋል በሚባሉት ወንጀል ለመክሰስ የሚያደርገውን ሙከራ ነቅፈዋል።
ፕሬዝደንቱን ለመክሰስ የፓርላማውን ሁለት ሦስተኛ ድምጽና የሕገ መንግስታዊውን ፍርድ ቤት ቢያንስ ስድስት ዳኞች ድጋፍ ማግኘት አለበት፡፡
በዋናው ተቃዋሚ የዲሞክራቲክ ፓርቲና በአምስት አነስተኛ ፓርቲዎች የቀረበው ፕሬዝደንቱን የመክሰስ ሐሳብ፣ ዓርብ ወይም ከዛ በኋላ ባሉት ቀናት ለድምጽ ሊቀርብ ይችላል ተብሏል።
የዩን ከፍተኛ አማካሪዎች እና ሐሃፊዎቻቸው በአንድነት ሥራ ለመልቀቅ ያመለከቱ ሲሆን፣ የመከላከያ ምኒስትራቸውን ጨምሮ የካቢኔ አባሎቻቸው ደግሞ ሥልጣናቸውን እንዲለቁ ተጠይቋል።
መድረክ / ፎረም