በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ኮሪያ አንድ ሆስፒታል ላይ በደረሰ ቃጠሎ አርባ አንድ ሰዎች ሞቱ

ደቡብ ኮሪያ ውስጥ በሚገኝ አንድ ሆፒታል ውስጥ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ፣ እስካሁን በተረጋገው መሠረት፣ 41 ሰዎች ሞቱ፣ ቁጥሩ ሊጨምርም ይችላል ተብሏል።

ደቡብ ኮሪያ ውስጥ በሚገኝ አንድ ሆፒታል ውስጥ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ፣ እስካሁን በተረጋገው መሠረት፣ 41 ሰዎች ሞቱ፣ ቁጥሩ ሊጨምርም ይችላል ተብሏል።

በቃጠሎው ከ70 በላይ ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን፣ አሥሩ በፅኑ የተጎዱ መሆናቸው ታውቋል።

ከዋና ከተማዋ ሲኦል 3መቶ ኪሎሜትር በስተደቡብ፣ ሚርያንግ ከተማ በሚገኘው ሰጆንግ ሆስፒታል ውስጥ ድንገተኛ ክፍል የተነሳው ቃጠሎ የጀመረው ዛሬ አርብ ማለዳው ላይ መሆኑም ተገልጧል።

የድንገተኛ አደጋ አስወጋጅ ቡድን ወደ ስፍራው በመሄድ እገዛ ያደረጉ ሲሆን፣ ወደ 2መቶ ያህል ህሙማንን የሚያስተናግደው የዚህ ሆፒታል 94 ሠራተኞችም በሙሉ በሰላም እንዲወጡ መደረጋቸው ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG