በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ኮሪያ ቴስላ ላይ የሀሰት ማስታወቂያ በማውጣት 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር መቀጮ ጣለች


ቴስላ
ቴስላ

ቴስላ የኤሌክትሪክ መኪናዎቹ የአየር ሁኔታ በሚቀዘቅዝበት ጊዜ መጓዝ የሚችሉበት ርቀት እንደሚቀንስ ገዢዎቹን ባለማስታወቁ 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር መቀጮ እንዲከፍል አዝዘናል ሲል የደቡብ ኮሪያ የንግድ ኩባኒያዎች ፍትሃዊ አሰራር ተቆጣጣሪ አካል አስታወቀ።

የኮሪያ ፍትሀዊ ንግድ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ናም ዶንግ ኢል ዛሬ በሰጡት መግለጫ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ መኪናዎች አምራቹ ኩባኒያ መኪናዎቹ ምን ያህል ርቀት እንደሚጓዙ፥ የሞተሩን አቅም የሚያጎለብተው ሱፐርቻርጀር ክንዋኔ እና የኤሌክትሪክ መኪናዎቹ ምን ያህል የነዳጅ ወጪ በመቀነስ ምን ያህል እንደሚጠቅሙ በተጋነነ መንገድ አስተዋውቋል" ብለዋል።

ኮሚሽኑ እንዳለው ከሆነ የቴስላ መኪናዎች ከባድ የአየር ቅዝቃዜ በሚኖርበት ጊዜ መነዳት የሚችሉበት ርቀት ኩባኒያው በኢንተርኔት ካስተዋወቀው ርቀት በግማሽ ሊቀንስ ይችላል።

ቴስላ ለዚህ ውንጀላ ወዲያውኑ የሰጠው ምላሽ የለም።

ይሁን እንጂ ለክረምት ጊዜ አነዳድ በዌብሳይቱ ላይ ባቀረባቸው ምክር አዘል መረጃዎች በሊላ የኃይል ምንጭ የመኪናውን ሙቀት ማስተካከል እና የመኪናውን የኤነርጂ አጠቃቀም በኩባኒያው መተግበሪያ አማካይነት መከታተል የሚል እንጂ የአየር ሁኔታ ከዜሮ በታች ሲወርድ ቴስላ መኪናዎች በተሞላላቸው ጉልበት የሚጓዙበት ርቀት እንደሚቀንስ አልተናገረም።

XS
SM
MD
LG