በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ኮሪያ ከአፍሪካ ጋራ ያላትን የልማት ትብብር እንደምታሳድግ አስታወቀች


የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝደንት ዩን ሱክ ዬዎል በጉባኤው ላይ
የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝደንት ዩን ሱክ ዬዎል በጉባኤው ላይ

አርባ ስምንት ከሚሆኑ የአፍሪካ ሃገራት መሪዎች ጋራ ጉባኤ ተቀምጣ የነበረችው ደቡብ ኮሪያ፣ በማዕድን፣ ኃይል እና የፋብሪካ ምርቶችን የተመለከቱ 47 ስምምነቶችን ተፈራርማለች፡፡

ደቡብ ኮሪያ ከአፍሪካ ጋራ ለመጀመሪያ ጊዜ ባካሄደችው ምክክር፣ ከ23 ሃገራት ጋራ ስምምነት ስትፈራረም፣ አህጉሪቱ ያላትን ሰፊ የማዕድን ሃብት እና የውጪ ንግድ ለመጠቀም በማለም እንደሆነ ተመልክቷል።

በዓለም ያለው የአቅርቦት ሰንሰለት በጂኦፖለቲካ ችግሮች ምክንያት እየተስተጓጎለ በመሆኑ፣ የአፍሪካ ሚና አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝደንት ዩን ሱክ ዬዎል በጉባኤው ላይ ተናግረዋል።

በማዕድን ረገድ ከአፍሪካ ሃገራት ጋራ ሽርክና መፍጠር እንደሚሹም ፕሬዝደንቱ ጨምረው ተናግረዋል።

ደቡብ ኮሪያ ለአፍሪካ የምታደርገውን የልማት ድጋፍ ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር ማሳደግ እንደምትሻና የውጪ ንግድን ለመደገፍና የደቡብ ኮሪያ ኩባንያዎች በአፍሪካ መዋዕለ ነዋይ እንዲያውሉም 14 ቢሊዮን ዶላር እንደመደበች ፕሬዝደንቱ አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG