በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንሶ ዞን ሦስት የማኅበረሰብ ፖሊስ አባላትን ጨምሮ ስምንት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ


በኮንሶ ዞን በሰገን ዙሪያ ወረዳ ሰገን ከተማ፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ ማንነታቸው ባልታወቁ የታጠቁ ግለሰቦች እንደተፈጸመ በተገለጸ ጥቃት፣ ሦስት የማኅበረሰብ ፖሊስ አባላትን ጨምሮ ስምንት ሰዎች መገደላቸውን፣ የወረዳው አስተዳደር ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል፡፡

በአካባቢው ከፍተኛ የጸጥታ ችግር መኖሩን የገለጹት የጋርዱላ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ኩናሎ በበኩላቸው፣ ጥቃት አድራሾቹ “ከአጎራባቹ የደራሼ ወረዳ የመጡ ናቸው” መባሉን አስተባብለዋል፤ “በዞኑ መንግሥት የሚደገፉ ናቸው፤” መባሉንም “ሐሰት ነው” ሲሉ አጣጥለዋል፡፡

በኮንሶ ዞን ሦስት የማኅበረሰብ ፖሊስ አባላትን ጨምሮ ስምንት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:42 0:00

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የሰገን ከተማ ነዋሪዎች፣ በሰው እና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ገልጸው፣ አሁንም በከፍተኛ ስጋት ውስጥ መኾናቸውን አመልክተዋል፡፡

በጥቃቱ የሞቱ ሰዎችን አስከሬን ለሁለት ቀን ማንሣት አለመቻላቸውን የተናገሩት ነዋሪዎቹ፣ ለክልሉ አስተዳደር እና ለፌዴራሉ መንግሥት የጸጥታ ኀይሎች የድረሱልን ጥሪ አቅርበዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG