በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብና በኦሮሚያ ክልሎች በተፈጠረ ግጭት 4 ሰዎች ተገደሉ


በደቡብና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ በሚገኙት አማሮና ሱሮ ባርጉዳ ወረዳዎች ውስጥ በተፈጠረ ግጭት አራት ሰዎች መገደላቸውን የአማሮ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

በደቡብና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ በሚገኙት አማሮና ሱሮ ባርጉዳ ወረዳዎች ውስጥ በተፈጠረ ግጭት አራት ሰዎች መገደላቸውን የአማሮ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የሱሮ ባርጉዳና የገላና ወረዳዎች አመራር አባላት “ወደ ህዝብ እንዳይወርዱ በኦነግ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል” ሲሉ የወረዳ ባለሥልጣናት ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ከስሰዋል።

ግጭቱ መኖሩን እንደሚያውቅና ባለሥልጣናቱ ከኦነግ ታጣቂዎች የተሰጣቸው ምንም ማስጠንቀቂያ እንደሌለ ለቪኦኤ የገለፀው የምዕራብ ጉጂ ዞን አስተደደር “የዞኑ የመንግሥት መዋቅር ህዝቡን እያስተዳደረ ነው” ብሏል፡፡

ጥቃቱን እየፈፀመ ያለው “ዘመናዊና ከባድ መሣሪያ የታጠቀ የኦነግ ኃይል ነው” ብለዋል ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው ነዋሪዎች፡፡

ከምዕራብ ጉጂ ዞን ገላናና ሱሮ ባርጉዳ ወረዳዎች አርብቶ አደሮችን ለማግኘት ያደረገው ጥረት አለመሣካቱን ሪፖርተራችን ዮናታን ዘብዴዎስ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

በደቡብና በኦሮሚያ ክልሎች በተፈጠረ ግጭት 4 ሰዎች ተገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:53 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG