በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋርዱላ ዞን ደራሼ ወረዳ ሰዎችን ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሰር ቀጥሏል” የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች


በጋርዱላ ዞን ደራሼ ወረዳ ሰዎችን ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሰር ቀጥሏል” የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:57 0:00

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ጋርዱላ ዞን፣ ደራሼ ወረዳ፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ ዘጠኝ ሰዎች ታስረዋል ሲሉ ነዋሪዎችና ቤተሰቦቻቸው ዛሬ መስከረም 23 ቀን 2017 ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ከዞኑ የተሰወሩ እና የት እንዳሉ የማይታወቁ 55 ሰዎች አሉ ሲሉም ተናግረዋል።

የደራሼ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ኪስሞ ኪታንቦ፤ በወንጀል የተጠረጠሩ "ቁጥራቸው በዛ ያለ ሰዎች በአከባቢው አለ ባሉት ወታደራዊ ዕዝ ኮማንድ ፖሰት መታሰራቸውን አምነዋል።

ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ያልቀረቡትም ጊዜው የአገሪቱ ፍርድ ቤቶች የእረፍት ጊዜ በመሆኑና የተጠርጣሪዎች ቁጥር በመብዛቱ ነው ሲሉ አስተዳዳሪው ጠቅሰዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG