በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"በሰሜንና ደቡብ ኮሪያ መካከል ሊጀመር ያለውን ድርድር ያነሳሳሁት እኔ ነኝ" ፕሬዚዳንት ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ ሐሙስ ባስተላለፉት መልዕክት፣ “በሰሜንና ደቡብ ኮሪያ መካከል ሊጀመር ያለውን ድርድር ያነሳሳሁት እኔ ነኝ” ሲሉ፣ ትዊት አደረጉ። ውለታው፣ “ለአስተዳደሬ ጠንካራና ፅኑ አመራር ሊሰጥ ይገባል” ሲሉም ተኩራርተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ ሐሙስ ባስተላለፉት መልዕክት፣ “በሰሜንና ደቡብ ኮሪያ መካከል ሊጀመር ያለውን ድርድር ያነሳሳሁት እኔ ነኝ” ሲሉ፣ ትዊት አደረጉ። ውለታው፣ “ለአስተዳደሬ ጠንካራና ፅኑ አመራር ሊሰጥ ይገባል” ሲሉም ተኩራርተዋል።

“አያሌ ጠበብት ሞክረውት ያልተሳካው ድርድር አሁን እውን ሲሆን፣ የእኔ ጥረት ያልገባበት ይመስላችኋልን?” ሲሉም ይጠይቃሉ ትራምፕ።

የሰሜኑ ፕሬዚደንት ኪም ጆንግ ኡን፣ ለደቡብ ኮሪያው የበጋ ኦሊምፒክ ልዑካንን እንደሚልኩ ካስታወቁ በኋላ፣ እአአ ከ2016 ጀምሮ በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል ተዘግቶ የቆየው ድንበር እንደሚከፈት ስምምነት መደረሱ አይዘነጋም።

ከድንበሩ መከፈት ቀጥሎም የሁለቱ አገሮች ልዑካን ለሃያ ደቂቃዎች ውይይት ማካሄዳቸውን ደቡብ ኮሪያ አስታውቃለች።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG