በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዙማ ከምርጫ ታገዱ


የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ጄከብ ዙማ
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ጄከብ ዙማ

የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ጄከብ ዙማ ከሁለት ወራት በኋላ በሚደረገው ምርጫ እንዳይሳተፉ የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን አግዷል።

ከስድስት ዓመታት በፊት ከሥልጣናቸው የተነሱት የ81 ዓመቱ ዙማ፣ የሙስና ክስ ተመስርቶባቸው የ15 ወራት እስር ተፈርዶባቸው ነበር።

ዙማ ሥልጣናቸውን ቢለቁም በአገሪቱ ፖለቲካ ሥፍራ ያላችውና አጨቃጫቂ ፖለቲከኛ ናቸው።

የሃገሪቱ ሕገ መንግስት ከ12 ወራት በላይ በእስር የተቀጣ ግለሰብ በምርጫ መካፈል እንደማይችል በመደንገጉ ዙማ ከመጪው ምርጫ እንደታገዱ የምርጫ ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ከአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲ) ፓርቲ ወጥተው “ምኮንቶ ሲዝዌ” (ኤምኬ) የሰኘ ፓርቲ ያቋቋሙት ዙማ፣ ከቀድሞው ፓርቲያቸውም ክሶች ተመሥርተውባቸዋል።

ዙማ የኤኤንሲ ፓርቲ አባላትን “ከሃጆች” ሲሉ ይከሳሉ። ፓርቲው በበኩሉ ዙማ የፓርቲውን ስም እንዳይጠቀሙ ፍርድ ቤት ጠይቋል።

ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያውን ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ካደረገችበት ከእ.አ.አ 1994 ወዲህ የሚደረግ ፉክክር የሚታይበት ምርጫ እንደሚሆን በመጠበቅ ላይ ነው።

በሥልጣን ላይ የከረመው ኤኤንሲ በአሁኑ ወቅት የሚያገኘው ድምጽ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ50 በመቶ በታች ይወርዳል ተብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG