በደቡብ አፍሪካ ሰሜን ክዋዙሉ ግዛት፣ ቶንጋት በተባለች ከተማ በደረሰ ከባድ አውሎንፋስ፣ በንትሹ ሰባት ሰዎች ሲሞቱ ከ1,000 በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡
የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ከተማዋ አውሎ ንፋስ በተቀላቀለበት ከባድ ዝናብ ክፉኛ የተጎዳች ሲሆን ነዋሪዎቹ ጉዳቱን ለማየት ትላንት ረቡዕ ወደቀያቸው ተመልሰዋል።
ዞንዶ የተባሉት የቶንጋት ነዋሪ " ከእንቅልፌ ስነቃ በሩን መክፈት አልቻልኩም፡፡ ምክንያቱም የቆርቆሮው ብረት ከውጭ በሩን ዘግቶታል፡፡ ብረቱን ጎተት ሳደርግ ኃይለኛ አውሎ ንፋስ ከፍተኛ ነጎድጓድ እና ከባድ ዝናብ አየሁ። በቤቴ ውስጥ እንዳለሁ ነው ከባዱ ዝናብ የወረደብኝ፡፡” ብለዋል፡፡
የአደጋው መከላከል ቡድን በመንግስት ህንፃዎች ውስጥ የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን ማስተናገድን ጨምሮ የደረሰውን የጉዳት መጠን በመገምገም አፋጣኝ እርዳታ እየሰጠ መሆኑ ተገልጿል፡፡
መድረክ / ፎረም