የቀድሞው ሚኒስትር የሞዛምቢክን ኢኮኖሚ ባሽመደምደው ግዙፍ የብድር ቅሌት እጃቸው አለበት ተብለው ተከሰዋል።
ባለፈው ታህሳስ ወር በጆሃንስበርግ በኩል ሲያልፉ የተያዙት የቀድሞው ሚኒስትር ማኑዌል ቻንግ የሃገሪቱም ኢኮኖሚ ባመሰቃቀለው የሁለት ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ቅሌት በተያያዘ በዩናይትድ ስቴትስም በሞዛምቢክም ይፈለጋሉ። ሁለቱም የጆሃንስበርግ ፍርድ ቤት ሚኒስትሩን አሳልፎ እንድትሰጣቸው ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱ ለፍትህ ሚኒስትሩ መርቶታል። ሚኒስትሩ ማይክል ማሱታ ባወጡት መግለጫ “ለፍትህ ስንል ወደሞዛምቢክ ቢላኩ የተሻለ ሆኖ አግኝተነዋል” ብለዋል።
የዩናይትድ ድስቴትስ ባለሥልጣናት በውሳኔው ላይ አስተያየት ለመስጥት ፈቃደኛ አልሆኑም።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ