ዋሺንግተን ዲሲ —
ደቡብ አፍሪካ ትናንት ሰኞ የደረሳት የመጀመሪያው የአስትራዜኔካ ሰራሽ የኮቪድ-19 ክትባት የሃገሪቱ የጤና ጥበቃ ተቆጣጣሪዎች ከፈተሹት በኋላ በጤና አገልግሎት ግንባር ላይ ላሉ ሰራተኞች እንደሚሰጥ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሴሪል ራማፎሳ አስታወቁ።
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ራማፎሳ ትናንት ጆሃንስበርግ አውሮፕላን ማረፊያ የደረሰውን የመጀመሪያውን አስራ ሁለት ሚሊዮን ክትባት ከሌሎች ባለሥልጣናት ጋር ሆነው ከተቀበሉ በኋላ ባሰሙት ንግግር በመጀመሪያ የጤና ሰራተኞች ይከተባሉ ብለዋል።
በማስከተል በሌሎች አስፈላጊ ህዝባዊ አገልግሎት ሥራዎች ላይ ያሉ ሰራተኞች እንዲሁም ዕድሜያቸው ከስድሳ ዐመት በላይ የሆኑ እንዲሁም በእንክብካቤ ቤቶች የሚጠበቁ ሰዎች እና የተለያዩ አባሪ የጤና ችግሮች ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ክትባቱን እንደሚያገኙ ነው ፕሬዚዳንቱ ያብራሩት።