በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ የሀገር ይዞታ መግለጫ ንግግራቸውን አያደርጉም

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ከነገ ወዲያ ሃሙስ ሊያደርጉ ታቅዶ የነበረ የሀገር ይዞታ መግለጫ ንግግራቸው ለሌላ ጊዜ ተላልፏል። ከሥልጣን እንዲወርዱ ተውጥረው ያሉት ዙማ ግፊቱ በርትቶባቸዋል።

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ከነገ ወዲያ ሃሙስ ሊያደርጉ ታቅዶ የነበረ የሀገር ይዞታ መግለጫ ንግግራቸው ለሌላ ጊዜ ተላልፏል። ከሥልጣን እንዲወርዱ ተውጥረው ያሉት ዙማ ግፊቱ በርትቶባቸዋል።

የሚስተር ዙማ ንግግር መዘግየቱን ዛሬ የፓርላማው አፈ ጉባዔ ባሌካ ሚቤቴ ኬፕ ታውን ውስጥ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ ፓርላማ ውስጥ የተሻለ የፖለቲካ ሁኔታ ማመቻቸት ይኖርብናል ብለን ነው ሲሉ አስረድተዋል።

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ

ባለፈው ታኅሣሥ ከገዢው የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ መሪነት የተነሱት ዙማ ሥልጣናቸውን እንዲለቅቁ ግፊቱ ተቀጣጥሎባቸዋል።

በሙስና የተለወሰው የፕሬዚዳንት ዙማ አስተዳደር ኤ ኤን ሲን የመራጭ ድጋፍ እንዲያጣ አድርጎታል።

ፓርቲው በአሁኑ ወቅት የሚመራው በምክትሉ ሲሪል ራማፎሳ ሲሆን ሲሆን ሁለቱ መሪዎች እና ደጋፊዎቻቸው ዙማ መቼ መሰናበት እንዳለባቸው ጭቅጭቅ ላይ ናቸው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG