በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ አፍሪካ እስላማዊ ታጣቂዎችን ለመዋጋት ወታደሮቿን ወደ ሞዛምቢክ ላከች


ፎቶ ፋይል፦ የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ መከላከያ ኃይሎች ወታደራዊ ኮንቮይ በፔምባ እአአ ኦገስት 5/2021
ፎቶ ፋይል፦ የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ መከላከያ ኃይሎች ወታደራዊ ኮንቮይ በፔምባ እአአ ኦገስት 5/2021

ደቡብ አፍሪካ እስላማዊ ታጣቂዎችን ለመዋጋት ወታደሮቿንና ጥይት የማይበሳቸው ተሽከርካሪዎቿን እንደአዲስ ወደ ሰሜን ሞዛምቢክ፣ ካቦ ዴልጋዶ ከተማ መላክ ጀምራለች።

ይህም ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ በደቡብ አፍሪካ ልማት ማኅበረሰብ (ሳዴቅ) የተጀመረው ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት አንዱ አካል መሆኑ ተገልጿል።

ከእስላማዊ መንግሥት ጋር ግንኙነት ካላቸው ታጣቂዎች ጋር ለመዋጋት እስካሁን ከ3ሺህ በላይ የሳዴቅ አባላት እና የሩዋንዳ ተዋጊዎች ወደ ሞዛምቢክ የተላኩ ሲሆን፣ ግጭቱ ከ3ሺህ ሰዎች በላይ ህይወት ሲያጠፋ ከ800 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።

ወታደሮቻቸውን ወደ ሞዛምቢክ ከላኩ የሳዴቅ አባል ሀገራት መካከል ቦትስዋና፣ ሌሴቶ፣ አንጎላ እና ዛምቢያ ሲገኙበት ሩዋንዳ በሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ፊሊፔ ኑሲ በተደረገላት ግብዣ ተጨማሪ ወታደሮችን መላኳ ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG