በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰው ሠራሽ ጸጉር እና 135 ሺህ ዶላር ጉቦ በመቀበል የተጠረጠሩ የደቡብ አፍሪካ አፈ ጉባዔ ሊከሰሱ ነው


ፎቶ ፋይል፦ አፈ ጉባዔዋ ኖሲቪዌ ማፒሳ-ንካኩላ በኬፕ ታውን የከተማው ማዘጋጃ ቤት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ንግግር ከማድረጋቸው በፊት ከጎናቸው ቆመው ይታያሉ፤ ኬፕታውን፤ ደቡብ አፍሪካ፣ እአአ የካቲት 10/2024
ፎቶ ፋይል፦ አፈ ጉባዔዋ ኖሲቪዌ ማፒሳ-ንካኩላ በኬፕ ታውን የከተማው ማዘጋጃ ቤት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ንግግር ከማድረጋቸው በፊት ከጎናቸው ቆመው ይታያሉ፤ ኬፕታውን፤ ደቡብ አፍሪካ፣ እአአ የካቲት 10/2024

የደቡብ አፍሪካ አቃቢያነ ሕግ የፓርላማ አፈ ጉባዔዋ የመከላከያ ሚኒስትር በነበሩበት ሦስት ዓመታት 135 ሺህ ዶላር እና ሰው ሠራሽ ጸጉር (ዊግ) በጉቦ መልክ ተቀብለዋል በሚል የሙስና ክስ ሊመሰርቱባቸው ማሰባቸውን አስታወቁ፡፡

አፈ ጉባዔዋ ኖሲቪዌ ማፒሳ-ንካኩላ ክስ ያልተመሰረተባቸው ወይም በቁጥጥር ስር ያልዋሉ ሲሆን "ባለሥልጣናቱ ስላቀረቡብኝ ውንጀላ በተገቢው መንገድ አላሳወቁኝም ወይም ትክከለኛውን አሠራር አልተከተሉም" ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡

አቃቢያነ ሕጉ ፍርድ ቤት ቀርበው መልስ የሰጡ ሲሆን አፈ ጉባዔዋ ራሳቸው ፖሊስ ጣቢያ እንዲቀርቡ አሳስበዋል፡፡

አፈ ጒባኤዋ ፖሊስ እንዳያስራቸው ጊዚያዊ እገዳ እንዲጣል ፍርድ ቤቱን የጠየቁ ሲሆን አቃቢያነ ሕጉ በበኩላቸው "የተለየ አስተያየት እንዲደረግላቸው እየጠየቁ ነው" ሲሉ ጥያቄውን ተቃውመዋል፡፡

ጉዳዩን የሚመለከቱት ዳኛ ሱሌት ፖተሪል ስለ እገዳው ጥያቄ እኤአ ሚያዝያ 2 ውሳኔ እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡ አፈ ጉባዔዋ አቃቤ ህግ ያሉትን ማስረጃዎችና ሰነዶችን በሙሉ እንዲያሳያቸው ጠይቀዋል፡፡

በችሎቱ የቀረበው ሰነድ የ67 ዓመቷ አፈ ጉባዔ እኤአ ከታህሳሰ 2016 እስከ 2019 ድረስ በድምሩ 135 ሺህ ዶላር የሚደርስ 11 ክፍያዎችን መቀበላቸውን እንደሚያሳይ አቃቢ ሕግ ተናግሯል፡፡

እኤአ የካቲት 2019 በዋናው የደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ከተገናኙት አንድ ሰው ብቻ 15 ሺ ዶላር እና አንድ ሰው ሠራሽ ጸጉር (ዊግ) መቀበላቸው በሰነዱ ተመልክቷል፡፡

መደለያውን የሰጣቸው ሰው ማንነት አልተጠቀሰም፡፡ አፈ ጉባዔዋ ምንም ጥፋት የለብኝም ሲሉ ተናግረዋል፡፡በአፈ ጉባዔዋ ላይ የቀረበው ውንጀላ እአአ ግንቦት 29 ለሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ እየተዘጋጀ ለሚገኘው ለገዥው የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ የቅርብ ጊዜው ቅሌት ተደርጎ ተወስዷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG