በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ የእስራኤል ኤምባሲ እንዲዘጋና የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዲቋረጥ ወሰነ


 የደቡብ አፍርካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ
የደቡብ አፍርካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ

እስራኤል በጋዛ የተኩስ አቁም ለማድረግ እስከምትስማማ ድረስ፣ በአገሪቱ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ እንዲዘጋ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲቋረጥ የሚጠይቀውን የውሳኔ ሀሳብ በመደገፍ አብዛኞቹ የደቡብ አፍሪካ ህግ አውጭዎች ትናንት ማክሰኞ ድምጽ ሰጥተዋል።

በገዥው የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ የተደገፈው ውሳኔ በፓርላማው የጸደቀው፣ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ፣ ከሌሎች የዓለም መሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት፣ “እስራኤል የሐማስ ታጣቂ መሪዎች ፍለጋ ጋዛ ላይ በምታካሄደው ወታደራዊ ጥቃት፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽማለች” ብለው በከሰሱበት ወቅት መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በተቃዋሚው ‘የኢኮኖሚ ነጻነት ተፋላሚዎች፣ ፓርቲ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ የ248 የፓርላማ አባላትን ድጋፍ ሲያገኝ 91 የህግ አውጭዎች ተቃውመውታል።

እስራኤል በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን በተገደሉባት ጋዛ የጦር ወንጀሎችን እየፈፀመች እንደሆነ ታምናለች።”

ፓርላማው ውሳኔውን የሰጠው፣ የእስራኤል የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በደቡብ አፍሪካ አምባሳደር የሆኑትን ኤልያቭ ቤሎቴርኮቭስኪን “ለምክክር” በሚል ወደ እየሩሳሌም መጥራቱን ከገለጸ በኋላ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

የእስራኤልና ደቡብ አፍሪካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በጋዛ ጦርነት ምክንያት ውጥረት የነገሠበት መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ራማፎሳ አገራቸው “እስራኤል በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን በተገደሉባት ጋዛ የጦር ወንጀሎችን እየፈፀመች እንደሆነ ታምናለች።” ሲሉ ከዚህ ቀደም በሰጡት መግለጫ መናገራቸውም በአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባ ተጠቅሷል፡፡

ደቡብ አፍሪካ “እስራኤል በጋዛ ፈጽማለዋለች” ባለችው “የዘር ማጥፋት” ወንጀል ዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎትእንዲመረምር መጠየቋን ባለፈው ሳምንት አስታውቃለች።

የአገሪቱ ካቢኔም፣ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ነታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ እንዲያወጣ ዓለም አቀፉን የወንጀል ፍርድ ቤት መጠየቁ ተዘግቧል።

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል የነበራትን አምባሳደር ያስጠራች ሲሆን ሁሉንም ዲፕሎማቶቿን ማስወጣቷም ተዘግቧል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG