በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ አፍሪካ ሆስፒታሎች ተጨማሪ የኮቪድ-19 ተጋላጮችን ለመቀበል እየተዘጋጁ ነው


በኦሚክሮን ቫይረስ ሳቢያ ለአራተኛ ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተመታቸው ደቡብ አፍሪካ ቁጥራቸው የበዛ ህሙማንን ለመቀበል ሆስፒታሎችዋን እያዘጋጀች መሆኑን የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራሞፎሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡

በደቡብ አፍሪካ ወደ 2ሺ300 የነበረው እለታዊው የኮቪድ-19 ተጋላጮች ቁጥር እየጨመረ መጥቶ ባለፈው ዓርብ ከ16ሺ በላይ መድረሱ ተገልጿል፡፡

ፕሬዚዳንት ራሞፎሳ ኮቪድ 19ን አስመልክቶ በየሳምንቱ በሚወጣው የዜና መጽሄት “በሃገሪቱ የኦሚክሮን ቫይረስ በአብዛኛው የሃገሪቱ ክፍል መነጋገሪያ የሆነ ይመስላል” ካሉ በኋላ ሰዎች እንዲከተቡ አሳስበዋል፡፡ በቂ የክትባት መድሃኒቶች መኖራቸውን ጠቅሰው ብዙ ሰዎች እየተከተቡ በሄዱ ቁጥር ብዙ የንግድ አገልግሎቶች እየተከፈቱ ይመጣሉ ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG