በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ አፍሪካ ተጨማሪ 8 የማዕድን ቆፋሪዎች አስክሬን ተገኘ


በደቡብ አፍሪካ የማዕድን ማውጫ የነፍስ አድን ሠራተኞ ዛሬ ማክሰኞ 8 ተጨማሪ አስክሬኖችን ከጉድጓዱ አውጥተዋል፡፡
በደቡብ አፍሪካ የማዕድን ማውጫ የነፍስ አድን ሠራተኞ ዛሬ ማክሰኞ 8 ተጨማሪ አስክሬኖችን ከጉድጓዱ አውጥተዋል፡፡

በደቡብ አፍሪካ የማዕድን ማውጫ የነፍስ አድን ሠራተኞ ዛሬ ማክሰኞ 8 ተጨማሪ አስክሬኖችን ከጉድጓዱ አውጥተዋል፡፡መውጣት ያልቻሉ ከ400 የሚበልጡ ቆፋሪዎች አሁንም ጉድጓዱ ውስጥ እንዳሉ ተነግሯል፡፡ የሞቱት ማዕድን ቆፋሪዎች ቁጥር 100 መድረሱም ተመልክቷል፡፡

በጎ ፈቃደኛ የነፍስ አድን ሠራተኞች በጉድጓዱ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ሁኔታ እየተከታተሉ ሲሆን ፖሊስ ህገ ወጥ የማዕድን ሠራተኞች ናቸው ያላቸውን ጉድጓዱ ውስጥ ያሉትን ቆፋሪዎች የግዳቸውን ሲወጡ ለማሰር የርዳታ አቅርቦት እንዳይገባላቸው መከልከሉን አስታውቋል፡፡

የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጨማሪ ሞት ለማስቀረት ባለፈው ቅዳሜና እሁድ ለማዕድን ቆፋሪዎቹ የምግብ፣ የውሃ እና የህክምና እርዳታ ያለማቋረጥ እንዲደርስ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

አንድ የሲቪክ ድርጅት ተወካይ ለሮይተርስ እንደተናገሩት ስለ ሁኔታው ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የድርጅታቸውን በጎ ፈቃደኞች ወደ ማዕድን ማውጫው ልከዋል።

የነፍስ አድን ሥራው የቀጠለው ባለፈው ሳምንት፣ "ስቃዩን አልቻልነውም እንደ ዝንብ እየሞትን ነው" በማለት የማዕድን ቆፋሪዎቹ ብጣቂ ወረቀቶች ላይ በጻፏቸው ደብዳቤዎች መማጸናቸውን ተከትሎ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG