በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ አፍሪካ በምርጫ ቀን መውጣት የማይችሉ ድምፅ ሰጡ


የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ለደጋፊዎች የኤፍኤንቢ ስታዲየም ንግግር አድርገዋል በጆሃንስበርግ፣ ደቡብ አፍሪካ
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ለደጋፊዎች የኤፍኤንቢ ስታዲየም ንግግር አድርገዋል በጆሃንስበርግ፣ ደቡብ አፍሪካ

በደቡብ አፍሪካ ረቡዕ ሊደረግ በታቀደው የምርጫ ቀን ድምፅ መስጠት የማይችሉ መራጮች ዛሬ ሰኞ ድምፅ ሲሰጡ ውለዋል።

በምርጫው ቀን ሥራ ላይ ለሚሆኑ፣ አካል ጉዳተኞችና ሌሎችም ልዩ ዝግጅት የሚያፈልጋቸው ሰዎች ዛሬ ድምፅ እንዲሰጡ ሲፈቀድ አጠቃላይ ሕዝቡ ግን ረቡዕ ወደ ምርጫ ጣቢያ ለማምራት ቀጠሮ ይዟል።

ዛሬ ድምፅ የሰጡት 1.6 ሚሊዮን እንደሚሆኑ ሲገመት፣ አጠቃላይ ድምፅ ሰጪዎች 27.6 ይሆናሉ።

የምርጫ አስፈጻሚዎች 624 ሺሕ የሚሆኑ አካል ጉዳተኞችን በየቤታቸው እየዞሩ ድምፅ እንዲሰጡ አድርገዋል።

የረጅም ጊዜ ገዢው ፓርቲ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤ ኤን ሲ) ተቀባይነት እያጣ መሆኑን የሕዝብ አስተያየት መለኪያዎች በማሳየታቸውና በዚህ ምርጫ በፓርላማ የበላይነትን ያጣል የሚል ግምት በመኖሩ ምርጫው ታሪካዊ ሊሆን ይችላል ተብሏል።

ኤ ኤን ሲ ባለፈው ቅዳሜ የመጨረሻውን የምርጫ ዘመቻ በአንድ ስቴዲየም አድርጓል። የሙዚቃ ዝግጅቱን ተከትሎ፣ ፕሬዝደንት ሰሪል ራማፎሳ ንግግር ሲጀምሩ የታዳሚው ቁጥር እየሳሳ መምጣቱን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG