በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ተያዦች ቁጥር ከግማሽ ሚሊዮን አሻቀበ


ደቡብ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ተጋላጮችዋ ቁጥር ከግማሽ ሚሊዮን ማለፉን ትናንት አስታውቀች

በዚህም መሰረት ደቡብ አፍሪካ በሃምሳ አራቱም የአፍሪካ ሃገሮች በጠቅላላ ከተረጋገጠው የቫይረሱ ተያዦች ቁጥር ከሃምሳ ከመቶ የሚበልጠውን ይዛለች

የደቡብ አፍሪካ የጤና ሚንስትር ትናንት ቅዳሜ ማታ አስር ሽህ አንድ መቶ ሰባት አዲስ የቫይረሱ ተጋላጮች መገኘታቸውን ጠቅሰው አጠቃላዩ ቁጥር አምስት መቶ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና እንደደረሰ ተናግረዋል፤ ከዚህ ውስጥ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ሃምሳ ሶስት ሰዎች በበሽታው ለህልፈት ተዳርገዋል

አጠቃላይ የህዝብ ቁጥሩዋ ወደሃምሳ ስምንት ሚሊዮን የሚሆነው ደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ ተጠቂዎች ብዛት ዩናይትድ ስቴትስን ብራዚልን ሩስያንና ህንድን ተከትላ አምስተኛነቱን ይዛ ትገኛለች

XS
SM
MD
LG