ዋሺንግተን ዲሲ —
አንድንድ የደቡብ አፍሪካ ሆስፒታሎች፣ በቂ የህክምና ሰራተኞችና መሣሪያዎች የሉንም በማለት፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ በኮሮናቫይረስ የተያዙ በሽተኞችን አንበቀልን እያሉ መሆናችው ተዘግቧል።
ፖርት ኤሊዝበት በሚገኘው ሆስፒታላቸው ውስጥ ያለው፣ በጸና የታመሙ ሰዎች የሚታከሙበት ክፍል ለመቀበል ያቻለው፣ ለህክምና ከመጡት አንድ አራተኛውን ብቻ ነው ሲሉ፣ ዶ/ር ቶቢሳ ፎዶ ተናግረዋል።
ይህ ሁኔታ ልብ የሚሰብር መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ፎዶ፣ በርካታ ሰዎች በህክምና እጦት ምክንያት እየሞቱ ናቸው ብለዋል።
ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ከ300,000 በላይ የሚሆኑ ኮሮናቫይረስ እንደያዛቸው በምርመራ የተረጋገጠ ሰዎች እንዳሉ፣ በሞት የተለዩት ደግሞ ከ4,400 በላይ እንደሚሆኑ ተገልጿል።