በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጃኮብ ዙማ ልጅ በሙስና ክስ ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ በዋስ ተለቀቀ


ዱዳዛን ዙማ
ዱዳዛን ዙማ

የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ልጅ በሙስና ክስ ዛሬ ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ በዋስ ተለቋል።

የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ልጅ በሙስና ክስ ዛሬ ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ በዋስ ተለቋል።

ዱዳዛን ዙማ ወደ ጆሀንስበርግ ፍርድ ቤት የተወሰደው በእግረ-ሙቅ ታስሮ ሲሆን ከውጭ ከተመለሰ ጥቂት ቀናት በኋላ ነው የተያዘው። የ $7,500 ዶላር ዋስ ከፍሎ ተለቋል። ጉዳዩ እስከ መጪው ጥር ወር ተላልፏል።

ዙማ የተከሰሰው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ከነብሩት ምከቢሲ ጆናስ ጉዳይ ጋር በተይያዘ ነው። ምከቢሲ የጆናስ ጉብታ ቤተሰብ የገንዘብ ሚኒስትር እንድሆን ጠይቆኝ ነበር ሲሉ ለአቃብያነ-ህግ ተናግረዋል። የጉብታ ቤተሰብ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ በሚያደርጉት የካቤኒ ሚኒስትሮች ስያሜ ላይ ተጽዕኖ ነበረው ተብሎ ይከሰሳል።

አባትየው ጃኮብ ዙማ የግል ቤታቸውን ለማደስ $20 ሚልዮን የመንግሥት ገንዘብ ተጠቅመውል የሚል ክስ በሚያካትቱ በርካታ የሙስና ክሶች ምክንያት ይመሩት በነበሩ የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ተገደው ባለፈው የካቴ ወር ከሥልጣን ወርደዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG