በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮሮናቫይረስ በደቡብ አፍሪካ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የደቡብ አፍሪካ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዛሬ 8 ተጨማሪ የኖቬል ኮሮናቫይረስ በሽተኞች መኖራቸውን አስታውቋል። በአጠቃላይ ቢያንስ 24 ደርሰዋል ማለት ነው።

የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ የተዛማች በሽታዎች ተቋም ሀገሪቱ የመጀመሪያው በሀገር ውስጥ የተላለፈ የኖቬል ኮሮናቫይረስን አይታለች ሲል ዘግቦ ነበር። ነገር ግን የተባለው ሰው በሽታው እንደሌለበት ገልፆ ለተሳሳተው ዘገባ በትዊተር ይቅርታ ጠይቋል።

እስካሁን ባለው ጊዜ በሀገሪቱ ኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ከውጭ ሀገራት የገቡ ናቸው። በአሁኑ ወቅት በሽታው በሀገሪቱ መስፋፋቱን የሚያሳይ ምልክት የለም ብሏል የሀገሪቱ ብሄራዊ የተዛማች በሽታዎች ተቋም

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG