በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ አፍሪካ ከተደረመሰው ሕንፃ ሰዎችን የማውጣት ተስፋ በመመናመን ላይ ነው


የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ከተደረመሰው ሕንፃ ሥፍራ በሥራ ላይ ጆርጅ፣ ደቡብ አፍሪካ
የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ከተደረመሰው ሕንፃ ሥፍራ በሥራ ላይ ጆርጅ፣ ደቡብ አፍሪካ

በደቡብ አፍሪካ ከሁለት ቀናት በፊት ከተደረመሰው ሕንፃ ሥር ሰዎችን በሕይወት የማግኘት ጥረቱ ዛሬም ቀጥሏል። ተስፋ እየተመናመነ ቢሆንም፣ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ዛሬ ረቡዕም ፍለጋቸውን ቀጥለዋል።

በደርዘን የሚቆጠሩ ሠዎች አሁንም ያልተገኙ ሲሆን፣ ሰኞ ዕለት በግንባታ ላይ የነበረው ሕንፃ ሲደረመስ ሰባት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

ጆርጅ በተሰነችው በሃገሪቱ ደቡብ በምትገኘው ከተማ በደረሰው የሕንፃ አደጋ፣ 75 ከሚሆኑት ሠራተኞች ውስጥ 29 የሚሆኑት ከፍርስራሹ ውስጥ ከነ ሕይወታቸው ወጥተዋል። ስድስቱ ለሕይወት አስጊ ሁኔታ ውስጥ ሲሆኑ፣ 16 የሚሆኑት ደግሞ ከበድ ያለ ሁኔታ ውስጥ ናቸው ተብሏል።

ሞሰስ ማላላ የተባለ የግንባታው ካቦ፣ ሕንፃው ከመደርመሱ በፊት ከባድ ድምፅ መስማቱን ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግሯል።

ሠራተኞቹ አንድ በአንድ ሲወድቁ መመልክተቱን ተናግሯል። በርካቶች አሁንም ተቀብረው ይገኛሉ።

ትናንት ማክሰኞ ማምሻውን አንድ ሰው ከነ ሕይወቱ ተጎትቶ ሲወጣ መመልከቱንና የደስታ እልልታ መስማቱን የኢኤፍፒ ዜና ወኪል ሪፖርተር ጨምሮ አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG