በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ 19 ሰው የገደሉ ታጣቂዎችን እያደነ ነው

ደቡብ አፍሪካ ሁለት መጠጥ ቤቶች ውስጥ ባለፉት ተከታታይ ቀናት ተኩስ ከፍተው ቢያንስ አስራ ዘጠኝ ሰው የገደሉ ተጠርጣሪዎችን እያደነ መሆኑን የሃገሪቱ ፖሊስ ገለፀ።

ትናንት፤ ዕሁድ ሌሊት ሶዌቶ ከተማ ውስጥ ወደሚገኝ ቡና ቤት ጠብመንጃና ሽጉጥ የታጠቁ ሰዎች ገብተው በመዝናናት ላይ በነበሩት ሰዎች ላይ እንዳገኙ ተኩስ ከፍተው አስራ አምስት ሰው መግደላቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

ቅዳሜ ምሽትም ከሶዌቶ በስተደቡብ ምሥራቅ በምትገኘው ፒተርማሪትዝበርግ ከተማ ውስጥ አጥቂዎች ተኩስ ከፍተው አራት ሰዎች ገድለው ስምንት ሰዎች ማቁሰላቸውን ፖሊስ አረጋግጧል።

ሁለቱ ጥቃቶች ግንኙነት አላቸው ብሎ የሚያስጠረጥር ምልክት እስካሁን እንደሌለ አንድ የፖሊስ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።

በሁለቱም ስፍራዎች ተጠርጣሪዎቹ ማምለጣቸውና በጥቃቶቹ ውስጥ የተሳተፉት ስንት ሰዎች እንደሆኑ ለጊዜው እንደማይታወቅ ቃል አቀባዩ አክለው አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG