በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ አፍሪካ ግጭት


ደቡብ አፍሪካ ሲካሄድ የቆየው ፀረ ፍልሰተኞች ግጭት ያደረስውን ጉዳት፣ መገምገም ጀምራለች።

የደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣኖች እንደሚሉት በግጭቶቹ የ10 ሰዎች ህይወት ጠፍቷል፣ በርካታም ቆሰለዋል። ግጭቱ ፍርሃት አስፍኗል። የንግድ እንቅስቃሴን አሽመድምዷል። ደቡብ አፍሪካ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ጋር ያላትን ግንኙነት አሻክሯል።

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጥቃቶቹን አውግዘዋል። ጥቃቱን ባለፈው እሁድ የጀምሩት መጤዎች የሥራ እድል እየተሻሙን ነው የሚሉ የጭነት መኪና ነጂዎችና ሌሎችም ሲሆኑ ግለሰብ ፍልሰተኞች ላይ ጥቃት አድርሰዋል። መኖርያ ቤቶችንና የንግድ ተቋማትን ዘርፈዋል፣ ጉዳትም አድርሰዋል።

“ማንኛውም ዓይነት የቁጣና የቀቢጸ-ተስፋነት መጠን እንዲህ አይነቱን ውድመትና የወንጀል ድርጊት እስከ መፈፀም የሚያደርስ አይደልም” ብለዋል ፕሬዚዳንቱ። በውጭ ተዋላጆች መኖርያ ቤቶችና የንግድ መደብሮች ላይ ጥቃት መፈፀም ይቅርታ ሊደረግለት የሚቻል ተግባር አይደለም። መጤ-ጠልነትና አለመቻቻልም በቀላሉ ሊታይ የሚችል አይደለም ሲሉ ራማፎሳ አስገንዝበዋል።

ከሞቱት 10 ሰዎች ሁለቱ የውጭ ተወላጆች ናቸው ብለዋል ፕሬዚዳንቱ። 423 ሰዎች መታሰራቸውን አክለው ገልፀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG